Ethiopia || ሰበር ዜና - 33 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ || Today News 2019 thumbnail

Ethiopia || ሰበር ዜና – 33 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ || Today News 2019

Posted on

Welcome to my channel I’m Abel Birhanu from Ethiopia if you subscribe my channel you get more benefits. news, blogging , information,vine …..all Entertainment are available in my channel subscribe now Telegram youtube Facebook /

15 thoughts on “Ethiopia || ሰበር ዜና – 33 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ || Today News 2019

 1. ፖሊስ አብይን በቁጥጥር ስር የሚያዉለው መቼ ነው? ኦነግ 14 ባንክ ከኦዲፓ ጋር ተመሳጥሮ ሲዘርፉ፣ እናቶች በኦነግ ሲደፈሩ፣ ህፃናት በኦነግ ሲገደሉ፣ ንፁህ ሰው በጃዋር አዛዥነት ተዘቅዝቆ ሲሰቀል፣ ህዝብ በኦነግ ሲፈናቀል፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳያውጅ ዛሬ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ በገለፀው በአማራ ህዝብ ላይ ማወጅ ምን ይባላል ? አማራ ንቃ!!!

 2. ኣቢና ኤሱ ሲደመሩ ኣሰብ ሳይሆን ሞት፡ እርስ በእርስ መጋጨት፡ ስደት መጥፎነት ነው ዝቅ ብላቹ ማሰብ ኣለባቹ ኢትዮጵያኖች እኛ በዚህ ሰኣት ሁሉም ነገር ሰልችቶኛል ኢሰያስ ኸነ ድራሹ ለማጥፋት ወስነናል

 3. ታሪክን የሚረሱ ለመድገም የተፈጠሩ ናቸው!

  (የቴዎድሮስና የአዝማሪ ጥል)

  የጎንደር አዝማሪ አፄ ቴዎድሮስን በነገር ሰይፍ አንጀታቸውን ሲቆርጠው ኖሯል – ከኮሶ ሻጭ ልጅነት ስድብ እስከ ባህሪያቸው አጉልነት አቃቄር በማውጣት

  በዚህም ቴዎድሮስ ከልጅነታቸው ጀምሮ በሆዳቸው የያዙትን ቂም ጊዜና ሁኔታን ሁሉ ተጠቅመው ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በአዝማሪ ጦስ(ለሃጥእ የመጣ — እንዲሉ።)በሚገባ በህዝቡም ላይ ተግብረውታል።

  -የጎንደር አዝማሪ ሁሉ በአሸማቃቂ ተረቡና ቧልቱ ህሊናቸውን ሲነሳቸው የኖሩ ቴዎድሮስ እንደምንም ብለው ፋሲል ቤተመንግስት ተቀምጦ ጎንደርንና ሰሜንን ሲገዛ የኖረውን የየጁ(ወሎ) መሳፍንት አንድ ባንድ በማሸነፍ ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ተበቅለዋል።

  -አንድ ጊዜ እሳቸው ወደ ጎጃም መዝመታቸውን የሰማው የጎንደር መሳፍንት አምጾ ይደራጅ ጀመር፡ ይህን የሰሙት ቴዎድሮስ ሌሊት ሰው በተኛበት ሲገሰግሱ አድረው ጎንደር ሲደርሱ የከተማው ሴት ግልብጥ ብሎ ወጥቶ በእልልታ አናወጠው። የህንንም የሰማው የሸመቀው ታጣቂ ሁሉ በየዋሻው ውስጥ ገባ።ቴዎድሮስም ግንቡንና ምሽጉን ቢፈልጉ አንድም ሰው አጡ።ለካ ትዝ ሲላቸው ሴቶቹ እልል ያሉት ባሎቻቸው የቴዎድሮስን መምጣት አውቀው ቦታ እንዲይዙ ኖሯል።በዚህም ቴዎድሮስ ተናደው ያቺ ማታ እልል ስትል የነበረች ሴት ሁሉ አምጡልኝ ብለው አንድ ሳትቀር በሳር ቤት ውስጥ አጉረው እሳት ለቀቁባቸው። ከተማዋንም እሳት ለቀቁባት።

  አንድ ጊዜም የደብረታቦርን ገበሬ አንድም ሳይቀር ሰብስቡልኝ ብለው ከሰበሰቡላቸው በኋላ ፡ቀኑን ሙሉ ሲቀጡ(እጅና እግሩን ሲቆርጡ) ውለው የተረፈውን በነጋታው ለመጨረስ ሲሄዱ ህዝቡ ብዙ ሆነ፡ በሉ ወደቤት አስገቡልኝ ብለው አዘዙ፡ ይሀኔ አንድ ህፃን የእናቱን ቀሚስ እየጎተተ ያለቅሳል። ቴዎድሮስም አይተው ምን ሆኖ ነው ይሄ ህፃን እንዲህ የሚያለቅሰው ብለው ይጠይቃሉ፡አንዱ ሰዉን ሲጠብቅ ያደረው አሽከራቸው መልሶ – ትናንትና ሜዳው ላይ ሌሊቱን ዝናብ እላዩ ላይ ሲጥል ስላደረበት አሁን እቤት የሚገቡት ለመተኛት መስሎት ቦታ እንዳይሞላ ቶሎ ለመያዝ ነው ብሎ መለሰላቸው። ቴዎድሮስም በፀፀት ስቅስቅ ብለው በማልቀስ አምላኬ ምናለ እኔን ገለህ ይህን ህዝብ ብታሳርፈው ብለው ተናገሩ።

  -በአንድ ወቅት የጎጃምን ገበሬ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲጨፈጭፉት ከርመው ስለነበር ሜዳው በሬሳ ተሞልቶ ነበር፡ የወቅቱ አዝማሪም

  “ሞጣ ቀራንዮ ምነው አይታረስ

  በሬሳላይ መጣሁ ከዚያ እስከዚህ ድረስ”

  በማለት በሃዘን አንጎራጓለች።

  -አንድ ገበሬ ከወታደራቸው መሳሪያ ቀምቶ ተያዘና እሳቸው ፊት ለቅጣት ቀረበ ፡ ቴዎድሮስም ያን ገበሬ በመድፍ ፊት ቆሞ እንዲተኮስበት በማድረግ ሰውነቱ ተበታትኖ ጠፍቷል

  -ያሰሩትን አስርሺ የየጁ ገበሬ በበረት አጉረው በውሃጥም እንዲያልቅ አድርገውታል

  -ራሳቸው በአንደበታቸው፡ፈጣሪ የላከኝ ለቅጣት ነው በልው ተናግረዋል

  -በነበራቸው ጥላቻ አንድም ቀን ፋሲል ቤተ መንግስት ገብተው አያውቁም ነበር

  -በኢትዮጵያም ታሪክ ቤተክርስቲያን ሳያሰሩ የቀሩ ብቸኛው ንጉስ አድርጓቸዋል

  ——

  በዚህም የተነሳ ህዝቡ በምላሹ፥–

  -ከቀንደኛ ተቃዋሚያቸው ውስጥ አለቃ ገብረሃና አንዱነበሩ

  -ወደሩቅ ቦታ ሲሄዱ ሚስታቸውን ተዋበችን ማንም ከማይደርስበት ዋሻ ደብቀው ነበር የሚሄዱት(ህዝቡን ይገድልብኛል ብለው ስለሚሰጉ)

  -ከመቅደላ ለማምለጥ ከገብርዬ(ፊታውራሪ ገብረሕይወት ጎሹ) ጋር ሲማከሩ፤ገብረሕይወት (ገብርዬ) ግን ያልጨፈጨፍነው አገር የታለና ወዴት እንሄዳለን ህዝብ አይምረንም ና እዚሁ አሟሟታችንን እናሳምር ብለው መለሱ

  -ቴዎድሮስ ከመቅደላ ሊያመልጡ ነው የሚል ወሬ ስለተወራ ገበሬው ሁሉ የተራራውን ዙሪያ አጥሮ እንዳያመልጡ ሲጥብቅ ስለነበር፡ቴዎድሮስ ሁለት ጊዜ ሞክረው ወደ ተራራው ጫፍ ተመልሰው ወጥተዋል(ገበሬው እጃችውን ይዞ ለጄነራል ናፒር ለማስረከብ ወስኖ ስለነበር )

  – እሳቸው ከተሰዉ በኋላ ሚስታቸውንና ልጃቸውን የሚያስጠጋ አንድም ሰው ስላልነበር በመሰደዳቸው ፡ሚስታቸው ጥሩወርቅ መንገድ ላይ አርፈዋል

  ======

  ወሪሳው ካሳ በተባለ መጽሃፍ ላይ እንደሰፈረው ደግሞ (በይትባረክ ግደይ በተፃፈ)

  -ቴዎድሮስን የጠላቸ አገር ነው፡ ህዝቡ፡መሳፍንቱ፡ቤተክህነቱ ወዘተ(ገፅ 402)

  -ሁሉም የአቴ ቴዎድሮስን ውድቀት በሚገባ ተረድተውት ነበር(235)

  – ጎንደር ከተማ ኖረው አያውቁም(ቤተ መንግስት ገብተው አያውቁም)

  ለአቡነ ሰላማ(የቅባት እምነት አራማጁ ግብፃዊ ጳጳስ) ትምህርት የማይገዛ ቢኖር – ከፍ ሲል ካንገቱ ዝቅ ሲል ከባቱ ይቆረጣል ብለው አዋጅ አስነገሩ(387)

  ዛሪም የሚታየው ከሴራ ፖለቲካው በከፋ መልኩ የአዝማሪ አጉል ቀረርቶና የጎጠኝነት እሽኮለሌ አንዱን ማህበረሰብ በሌላው የመገለልና የመገፋት ስሜት እየፈጠረ ያለ ፡ በግልጽ የሚታይ የጎጠኝነት ትምክህት ዋጋ ያስከፈለ በመሆኑ ኪነጥበባችንንና የአዝማሪ ቤት ዳንኪራችንን ከአግላይነት ወደ አቃፊነት ጥበብ መመለስ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዋና ጉዳይ ነው።

  ለነገሩ መንግስቱ ሃይለማሪያምም – ጭካኔ ያበዛ የነበረው የሰፈሩ ልጆች ሲሰጡት በኖሩት ቦታና ግምት የተነሳ — ቾንቤ፡ ባሪያው የሚሉት ተቀፅላዎች— ትልቅ ከሆነም በኋላ ራሱ ሳይቀር በአንደበቱ ይናገረው የነበረው ፥ “ ፀጉረ ከርዳዳ፡ ከንፈረ ደንዳና፡ ዘጠኝ ጎድን — ” የመሳሰሉ መለዮዎች በውስጡ ቂምና ጥላቻ አብረውት እንዲያድጉ በመደረጉና ለማንነቱና ባህሪው አሉታዊ ተፅዕኖ ስለነበራቸው ነው የሚሉ አሉ።

  ሰላም ለኢትዮጵያ፡ ፍቅር ለሁላችን!

  ሰላምን እንግዛ፡እንከተላትም!

Leave a Reply

Your email address will not be published.